Fana: At a Speed of Life!

ተገጣጣሚ ቤቶች በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያግዛሉ – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የተገጣጣሚ ቤት የፈጠራ ቴክኖሎጂ ስራን ጎብኝተዋል፡፡

ቴክኖሎጂው በመዲናዋ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

በአነስተኛ ወጪና ጊዜ ቤት መገንባት ከማስቻል ባለፈ አካባቢው ለልማት ቢፈለግ በቀላሉ በማንሳት ሌላ ቦታ መስራት ያስችላል ብለዋል፡፡

በኮንስትራክሽን እና ግንባታ ዘርፍ ተመርቀው የተቀመጡ እና ፍላጎት ያላቸውን ወጣቶች በማሰልጠን የስራ ዕድል እንዲፈጠር የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ በብዛት እንዲስፋፋ የሚፈለገዉና በቅርቡ የተጀመረው የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤት እድሳት በጥቅም ላይ እንዲውል በቅንጅት እንሰራለንም ነዉ ያሉት ከንቲባዋ፡፡

ሚኒስቴሩ ÷ መሰል ቴክኖሎጂ በማፍለቅ እና ስታንዳርድ በማውጣት የህብረተሰቡን ችግር እንዲፈታ ይሰራል ያሉት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ናቸዉ፡፡

በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች የመኖሪያ ቤት ችግርን የመቅረፍ እና ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር በመሆኑ የክልል ከተሞች ቴክኖሎጂውን እንዲጠቀሙ ይደረጋልም ብለዋል፡፡

ተገጣጣሚ ቤቶቹ አስተማማኝ እና በአነስተኛ ወጪ በአጭር ጊዜ መጠናቀቅ የሚችሉ መሆናቸውን የቴክኖሎጂው አፍላቂ ኢ/ር ብርሀኑ ካሳ ገልጸዋል፡፡

የመገጣጠሚያ ቤቱ ያለምንም ኮለን እና ሌሎች የግንባታ ግብዓት ሳያስፈልግ በኮንክሪት እና በቃጫ ብቻ ቤት መስራት የሚያስችል ቴክኖሎጂ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክረታሪ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.