Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በሩብ ዓመቱ ከ70 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ70 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡
በሩብ ዓመቱ 76 ቢሊየን 845 ሚሊየን 591ሺህ 516 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ÷ 70 ቢሊየን 110 ሚሊየን 735ሺህ 068 ብር መሰብሰብ መቻሉን ነው የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው የገለጹት፡፡
በሩብ ዓመቱ ይሰበሰባል ተብሎ ከተያዘው እቅድ አንጻር 91 ነጥብ 24 በመቶ መፈጸም መቻሉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አፈጻጸሙም÷ ከሀገር ውስጥ 38 ቢሊየን 685ሚሊየን 792ሺህ 566 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ÷ 38 ቢሊየን 762 ሚሊየን 448 ሺህ 101ብር፣ ከውጭ ንግድ ታክስና ቀረጥ 38 ቢሊየን 106 ሚሊየን 984 ሺህ 548 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ÷ 31ቢሊየን 277ሚሊየን 213ሺህ 150 ብር መሰብሰብ ተችሏል ነው የተባለው፡፡
በተጨማሪም ከሎተሪ 71ሚሊየን 073 ሺህ 815ብር መሰብሰቡንም አቶ ላቀ ተናግረዋል፡፡
አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በሀገር ውስጥ ታክስ የ8 ነጥብ 54 በመቶ፣ በውጭ ንግድና ቀረጥ የ13 ነጥብ 4 በመቶ እድገት÷ በአጠቃላይ ከ6 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ወይም የ10 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ እንዳለው አሳውቀዋል፡፡
የእቅድ አፈጻጸሙ የኮሮና ወረርሽኝ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የንግድ ማጭበርበር እና የትግራይ እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎች ያሉ ችግሮች ባሉበት የተገኘ በመሆኑ አበረታች መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ግብር ከፋዮችም በታማኝነትና በወቅቱ ግብራቸውን በመክፈል እስካሁን እንዳደረጉት ሁሉ ከተቋማችን እና ከሃገራቸው ጎን እንዲቆሙ አቶ ላቀ አያሌው ጥሪ ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.