Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የወባ በሽታ መከላከል መርሃ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወባን ማጥፋት ከእኔ ይጀምራል በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው የንቅናቄ መርሃ ግብር ከክልል እስከ ቀበሌ አካባቢን በማጽዳትና የህዝቡን ግንዛቤን በሚያሳድግ መልኩ የሚከናዎን መሆኑ ተገልጿል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮት ጋትዊች የወባ በሽታ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ቀዳሚ የጤና ችግር ነው ብለዋል።
በሽታው ችግር የሚያደርሰው በተለይም በክረምቱ መግቢያና መውጫ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
ህብረተሰቡ የወባ መራቢያ አካባቢዎችን በማጽዳት፣ አጎበርንና ሌሎች የመከላከያ ዘዴዎችን በመጠቀም በሽታውን መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል።
ከጤና ሚኒስቴርና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የወባ በሽታን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ ነው ማለታቸውን የጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.