Fana: At a Speed of Life!

የጃፓን ባለሃብቶች የኢትዮጵያን የኢነርጂ ዘርፍ ማልማት እንደሚፈልጉ አምባሳደሯ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም ጃፓን በጃይካ በኩል ለኢትዮጵያ እያደረገች ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን አውስተዋል፡፡
 
በተለይም በክልሎች የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሳደግ ጃፓን እያደረገች ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
ኢትዮጵያ በውሃ ልማት ስራዎችና ከጸሃይ ሃይል ማምረት በሚያስችሉ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት ያላትን ፋላጎትም አስረድተዋል፡፡
 
በዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ የጃፓን ባለሃብቶችም አስፈላጊው ትብብር እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡
 
አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው÷ ጃፓን በንፋስ ሃይል፣ በውሃ ቴክኖሎጂ እንዲሁም በካይዘን አሰራር ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግ አስረድተዋል፡፡
 
በኢነርጂ ዘርፍ የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ማልማት እንደሚፈልጉ መግለጻቸውንም ከሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.