Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ነዋሪዎች የኮቪድ-19 ክትባትን ለመከተብ ያላቸው ተነሳሽነት ዝቅተኛ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት በነጻ እንዲሰጥ ቢመቻችም ህብርተሰቡ ለመከተብ ያለው ተነሳሽነት ዝቅተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገለጸ።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ÷ በሌሎች የዓለም ሀገራት አንድ ሰው ሥራ ለመቀጠር እና አገልግሎቶችን ለማግኝት የኮሮና ቫይረስ ክትባት መከተብ እንደ ግዴታ እየተወሰደ መምጣቱን አንስተዋል፡፡

ይህንን ልምድ በሀገራችን ተግባራዊ ለማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመምከር መታቀዱን ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስም ከ330 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ክትባቱ በነጻ መሰጠቱን ነው የተናገሩት፡፡

ለከተማዋ ነዋሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ለመስራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየመከሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኮቪድ 19 ክትባት መከተብ በቫይረሱ ላለመያዝ ያለው ጠቀሜታ ጉልም መሆኑን ያነሱት ሃላፊው ÷ በቫይረሱ ከሚሞቱት ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ክትባቱን ያልወሰዱ መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡

ስለሆነም ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ዜጋ ክትባቱን እንዲከተብ ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

ኮቪድ-19 በሀገራችን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ያስከተለ ወረርሽኝ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የጥንቃቄ መንገዶችን እንዲተገብርም አሳስበዋል።

በከተማ አስተደደሩ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት አብዛኛዎቹ መምህራን ክትባት መከተባቸውንም ጤና ቢሮው አስታውሷል።

በሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.