Fana: At a Speed of Life!

ሽብርተኛው ህውሃት ከራያ ወጣቶች ተቃውሞና እምቢተኝነት ገጠመው

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኛዉ ህውሃት በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የራያ ወጣቶችን ቤት ለቤት እየዞረ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የከፈተዉን ጥቃት እንዲቀላቀሉ ለማስገደድ ጥረት ቢያደርግም ተቃዉሞና እምቢተኝነት እንደገጠመዉ ምንጮቻችን ከስፍራዉ ዘግበዋል፡፡
በህግ ማስከበር ዘመቻው ግዜ የታጠቁ የራያ ተወላጅ የሆኑ ምልሻዎች ጁንታው ራያ ሲገባ ትጥቅ ፍቱ ሲባሉ አንፈታም በማለት በደቡባዊ ዞን በኩኩፍቶ ከተማ በላይ (በምእራብ በኩል) እሚገኝ ተራራ ወደ ሀሸንጌ እና ኮረም የሚያስወጣ ጫካ ላይ በርካታ የራያ ተወላጅ የሆኑ ምልሻዎች የተደበቁ ሲሆን ጁንታው በተደጋጋሚ ሽማግሌ በመላክ ትጥቅ እንዲፈቱ አልያም ወደ እሱ እንዲቀላቀሉ ቢጠይካቸውም እንዳልተሳካለት እና አሁንም ጫካ ውስጥ እንዳሉ ለመረጃዉ ቅርበት ያላቸዉ ምንጮቻችን ከስፍራዉ አረጋግጠዋል።
ሽብርተኛዉ ህውሃት የራያ ወጣቶችን ቤት ለቤት እየዞረ በግዴታ ወደ ጦርነት እንዲገቡ ለማድረግ ቢሞክርም ወጣቶችም እየጠፉ በየማሽላው እና በየጫካው፣ በየበረሃው እየተደበቁ እንደሆነ ምንጮች አረጋግጠዋል።
በተጨማሪ ጁንታው የራያን ህዝብ በግዴታ ብር እንዲያዋጡ እና ሁለት ሁለት ሰው እየሆኑ አንድ በሬ ገዝተው ለጁንታው እንዲያስረክቡ እያስገደዳቸው እንደሆን ምንጮች ገልፀዋል። ህብረተሰቡም በዚህ በመማረር አካባቢውን በመልቀቅ እየተደበቀ ያለበት ሁኔታ መኖሩ ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.