Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው ህወሓት 832 ትምህርት ቤቶች ወድመዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፈጸመው ወረራ በሰሜን ወሎ ዞን ብቻ 832 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ፡፡
አሸባሪው ቡድን በዞኑ በፈጠረው ችግር በእነዚህ ትምህርት ቤቶች በ2014 ዓ.ም መማር የነበረባቸው ከ330 ሺህ 600 በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ለመሆን መገደዳቸውን የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰጠ ታደሰ ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡
ሁሉም ትምህርት ቤቶች ሃብትና ንብረታቸው በመዘረፉ እና ህወሓት የጦር ካምፕ አድርጓቸው ስለነበር መማር ማስተማሩን በቅርብ ለመጀመር ፈታኝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አርሶአደሩ በክረምቱ የእርሻ ወቅት በሚገባ ሥራውን ማከናወን አለመቻሉንና የደረሱ ሰብሎችም በአሸባሪው ቡድን መጨፍጨፋቸውን እና መዘረፋቸውን አስረድተዋል።
በዞኑ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል ከ265 ሺህ በላይ የሚሆኑት የትምህርት ቤት ምገባ እንደሚያስፈልጋቸውም ምክትል ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
የሽብር ቡድኑን በተባበረ ክንድ በመደምሰስ አካባቢውን በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ ነፃ ማድረግ ጊዜ የሚሰጠው አለመሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የባከነውን የትምህርት ጊዜ በሚያካክስ መልኩ ወደ ሥራ ለመግባትም መንግሥት፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ሕዝቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.