Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ችግር አፍሪካዊ እልባት እንዲያገኝ ኢትዮጵያ ግፊት ማድረግ ይኖርባታል – ዶ/ር ሙከረም ሚፍታህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን አሁናዊ ችግር አፍሪካዊ በሆኑ ተቋማት መፍትሄ እንዲያገኝ ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት ማድረግ እንዳለባት በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ሙከረም ሚፍታህ ገለጹ።
ተመራማሪው ሚፍታህ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ፥ የሱዳን አሁናዊ ችግር ለሱዳን ሕዝብ አደገኛ ነው።
ይህ ሁኔታም ኢትዮጵያንም እንደ አገር ያሳስበታል ነው ያሉት።
ይህ አሁናዊ ችግር አፍሪካዊ በሆኑ ተቋማት መፍትሔ እንዲያገኝ ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት ማድረግ እንዳለባትም አንስተዋል።
ከሱዳን አሁናዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሱዳን ሕዝብ ጎን መቆሙ ተገቢ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በሱዳን የተከሰተውን ችግር የሕዝቡ ፍላጎትና ስሜት ባገናዘበ መልኩ ለመፍታት ከውጭ ጣልቃ ገብነት ይልቅ በአፍሪካዊ ተቋማት ችግሩ እንዲፈታ ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት በማድረግ ለሱዳን ሕዝብ አጋርነቷን ማሳየት እንደሚኖርባትም አመላክተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.