Fana: At a Speed of Life!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለመደገፍ ዝግጁ ነኝ አለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሰሶዎች የሆኑትን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ሥራ ዕድል ፈጠራ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ የሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሱሳ በ18ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ ላይ እንደገለጹት÷ ተቋማቸው የኢትዮጵያን አገራዊ የዲጂታል እድገት ለውጥ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የሚጠበቅበትን ይወጣል፡፡
የተቋሙ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ኃላፊ ማቲው ሀርቪ ሀሪሰን እና የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና የቴክኖሎጂ ኃላፊ ፔድሮ ራባካል በበኩላቸው÷ ሁሉም ዜጎች ከዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ጋር የጋራ የባለቤትነት ስሜት እንዲኖር ለማድረግ ለዲጂታል ክህሎት ስልጠናዎች ትኩረት እያየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፥ በቀጣይም ኔትወርኩን በጋራ ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አውስተዋል።
በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የኔትወርክ እና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎች ዝግጅት ወቅት መንግስት ላደረገው ትብብር ደስተኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ሁሉንም የኢንዱስትሪው አካላት ያካተተ፣ በመደጋገፍና ተጠቃሚነት በሚረጋገጥበት ሁኔታ ሥነ ምህዳሩን መገንባት እንደሚፈልጉ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ያኘነው መረጀ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.