Fana: At a Speed of Life!

በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ጥራት ችግርን ለማሻሻል በትኩረት መስራት ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከከፍተኛ ትምህርት አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን ለማዘመን መንግስት ትኩረት እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲዎቹም የአስተዳደር እና የመሰረተ ልማት ችግሮች እንደሚስተዋሉ ሚኒስትሩ አንስተዋል።

አብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ጥራት ጋር በተያያዘ የሚነሳባቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲችሉ ያሉባቸውን ክፍተቶች በአፋጣኝ ለይተው የመፍትሄ እርምጃዎችን እንዲወስዱም መመሪያ ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲዎች የፖለቲካ አቋም አራማጅ መሆን እንደሌለባቸውም አሳስበው ÷ከመንግስት ተጽዕኖ ነጻ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት ዩኒቨርሲቲዎቹ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባ መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.