Fana: At a Speed of Life!

ፌዴራል ፖሊስ ስራዎቹን ለማዘመን ከእንግሊዝ መንግስት ጋር ስምምነት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ አስተዳደር ልማት ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ነብዩ ዳኜ ለኢትዮጵያ፣ ለጅቡቲ እና ለአፍሪካ ህብረት የእንግሊዝ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ጉስ ማክገሊቨር እና የእንግሊዝ የሰላም ድጋፍ ሰጪ የአፍሪካ አማካሪ ስቲቭ ኦዴንግ ጋር በጋራ መስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በውይይታቸው የሰብዓዊ ደህንነትን ለማስጠበቅ፣ የፖሊስ አገልግሎትን ለማዘመን፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የወንጀል መከላከልና የወንጀል ምርመራ ስራ እንዲኖር ለማስቻል፥ እንዲሁም የፖሊስ አቅም ግንባታ ስራ ላይ በመደጋገፍ አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ነቢዩ ዳኜ ፖሊስነት የራስ ዜጎች ብቻ ሳይሆን የሰው ዘር ሁሉ ወንጀል እንዳይገጥመውና በሰላም እንዲኖር ሌት ከቀን የሚሠራበት ትልቅ መስዋእትነትን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።
ለሰላማችን ስንል ከሌሎች ሀገራት ልምድ እና ተሞክሮዎችን በመውሰድ፥ በትብብርና በጋራ ለመስራት የፖሊስ አልግሎት መጎልበት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለውም ነው የተናገሩት፡፡
የእንግሊዝ መንግስት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ከማጎልበት አኳያ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሰላም ማስከበር እና በወንጀል መከላከል ተግባራት ላይ ለሚያደርጋቸው ጥረቶችና ክንውኖች የነበረውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.