Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ሲኖዶሱ ለተፈናቀሉ ወገኖች 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉና ለችግር ለተዳረጉ ወገኖች 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳልፏል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ባካሄደዉ ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ወደ እግዚአብሔር መጸለይ አስፈላጊ በመሆኑ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፀሎት መርኃ ግብር እንዲካሄድ ወስኗል ነው ያሉት።
በአውስትራሊያ፣ ካናዳ ፣ አውሮፓ እና በአሜሪካ ውስጥ ሆነዉ ሕዝባዊ አንድነትን ለማፈራረስ የሚጥሩ በሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ማቅረቡን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከዚህ በፊት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን ያነሱት ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ አሁንም የሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ወስኗል ብለዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.