Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በጅቡቲ ከተመድ ተጠሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በጂቡቲ ከተባበሩት መንግስታት ተጠሪ ኤሪክ ኦቨርቬስት ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ብርሃኑ በዚህ ወቅት ስለ ኢትዮጵያና ጂቡቲ ታሪካዊ፣ ስትራቴጂያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ በመንገድ ግንባታና እና በባቡር ሀዲድ ዝርጋታ እየተጠናከረ የመጣውን የሁለቱን ሀገራት የትራንስፖርት ግንኙነትም አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ በአሸባሪው ህወሓት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አብራርተዋል።

አምባሳደሩ አንዳንድ ተቋማትና ሀገራት የአሸባሪውን እኩይ ተግባር ለመኮነን ቸልተኝነት ማሳየታቸውን አንስተዋል።

ህወሓት በሰሜን እዝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንደፈፀመ፣ እንዲሁም የአንድ ወገን የተኩስ አቁሙን በመተላለፍ በአማራና በአፋር ክልሎች ዜጎችን እንደጨፈጨፈና የንብረት ውድመት ማድረሱን አመላክተዋል።

ቡድኑ ጥቃት ለመፈጸም በሚንቀሳቀስበት ጊዜ እርዳታ ለማድረስ የሄዱ ተሽከርካሪዎችን ሲጠቀም እንደነበር በመጥቀስም፥ በተቃራኒው ተቋማቱና ሀገራቱ በኢትዮጵያ ላይ ያልተገቡ ጫናዎች እንዲደረጉ መንቀሳቀሳቸውንም አውስተዋል።

በጂቡቲ የተመድ ተጠሪ ኤሪክ ኦቨርቬስት በበኩላቸው ÷ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው ጉዳዩ በሠላማዊ ድርድር መፍትሄ እንዲያገኝ እንደሚጥሩ እና የሚሊየኖችን ህይወት አደጋ ላይ የጣለው ሁኔታ እልባት እንዲያገኝ በትብብር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.