Fana: At a Speed of Life!

ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለሚያሰማሩ ሀገራት በተዘጋጀ ጥናት ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በተባበሩት መንግስታት ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ በየአራት አመቱ ለሚያሰማሩ ሀገሮች በተዘጋጀ የዳሰሳ ጥናት ላይ ውይይት ተካሄደ።
የሰላም ማስከበር ማዕከል ለ2 ቀናት ባዘጋጀው መርሃ ግብር የመከላከያ ሰላም ማስከበር ከፍተኛ መኮንኖች እና አመራሮች እንዲሁም ከተባበሩት መንግስታት የተውጣጡ ልዑካን ቡድን ውይይቱን በጋራ አድርገዋል።
ጥናቱ በቅድመ ስምሪት ዝግጅትና በሰላም ማስከበር ስምሪት ወቅት ስለሚኖሩ የነፍስ ወከፍ ትጥቅና አልባሳት፣የሀገር ውስጥ ትራንስፖርት አገልግሎት ፣በህክምና፣የምግብና የቀን ውሎ አበል እንዲሁም የቅድመ ስምሪት ስልጠና ወጭና የመሳሰሉትላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።
የልዑካን ቡድኑ ዳይሬክተር ሚካኤል ሙሊንጌ ኪቲቪ ፥ የዳሰሳ ጥናቱ በኢትዮጵያ የተደረገበት ዋናው ምክንያት ኢትዮጵያ ለሰላም ማስከበር በምታሰማራው የሰው ሃይልና በምትፈፅመው ውጤታማ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በቀደምትነት ከሚጠቀሱት ሀገራት አንዷ በመሆኗ ነው ብለዋል።
የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማእከል ሃላፊ ተወካይ ብ/ጄኔራል መኮንን አስፋዉ ፥ የዚህ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ለሰው እና ለቁሳዊ ሃይል የሚወጡ ወጭዎች ምክንያታዊና ወጭ ቆጣቢ እንዲሆኑ ለማስቻል አስተዋፅኦ እንደሚያደርግና የተሻለ ግብአት እንደሚያመጣም መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.