Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በግሉ ዘርፍ የሚመራ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት አስቻይ ሁኔታዎችን እየዘረጋች ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ምንዛሬ ግኝት እና አካታችነትን ታሳቢ ያደረገ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ አስታወቁ።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለ2 ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 18ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ስብሰባ ተጠናቅቋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ÷የስራ እድል ፈጠራ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እና አካታችነትን ታሳቢ ያደረገ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢንተርኔት ግንኙነትን ማሻሻል፣ የመንግስት አገልግሎቶችን ኦንላይን ማድረግ፣ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት መዘርጋት፣ የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፣ የቴሌኮም ዘርፍ ማሻሻያ መንግስት በትኩረት እየሰራባቸው መሆኑን አብራርተዋል።

በኤሌክትሮኒክስ የመንግስት አገልግሎት ስራ ውስጥ በ40 የመንግስት ተቋማት በለሙ 200 የኦንላይን አገልግሎቶች ከ2 ሚሊየን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ጠቅሰዋል።

የፀደቀው የትራንዛክሽን አዋጅ፣ በረቂቅ ላይ ያሉ የዴታ ጥበቃ አዋጅ፣ የስታርትአፕ አዋጅ፣ የኢኖቬሽን ፈንድ፣ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳ በዘርፉ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራባቸው ያሉ የትኩረት መስኮች ናቸው።

“የብሄራዊ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን አጀንዳን ማፋጠን” በሚል በኢኖቬሽናን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ኤክስቴንሽያ ትብብር በተዘጋጀው በዚህ ጉብኤ ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት መሳተፋቸዉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.