Fana: At a Speed of Life!

ሸኔ እና ሕወሓትን በፋይናንስ፣ በቁሳቁስና መረጃ ሲደግፉ የነበሩ 88 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዳማ ከተማና አካባቢዋ ለአሸባሪዎቹ ሸኔ እና ሕወሓት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበሩ 88 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።
የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአካባቢ ሰላምና ፀጥታ ማስከበር ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ከበደ ለገሰ ለኢዜአ እንደገለጹት ፥ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት አሸባሪዎቹን በፋይናንስ፣ በቁሳቁስና በመረጃ በመደገፍ ሀገር ለማፍረስ በሚያደርጉት እቅስቃሴ ውስጥ መሳተፋቸውን በጥናት ተለይቶ ነው።
የፀጥታ ሃይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ባደረገው እንቅስቃሴ ሰሞኑን 88 ተጠርጣሪዎችን በመቆጣጠር ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
አዳማ በቀን ከ100 ሺህ ህዝብ በላይ የሚወጣባትና የሚገባባት ከተማ ናት ያሉት ኮማንደር ከበደ፥ ሰርጎ ገቦች አጋጣሚውን ተጠቅመው ሾልኮው እንዳይገቡ የፀጥታ አካላት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በከተማዋ መግቢያና መውጫ በሮች 24 ሰዓት ክትትል፣ ቁጥጥርና ፍተሻ እያደረጉ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
በዚህም ጥሩ ውጤት ተገኝቷል ያሉት ኮማንደሩ፤ ስምንት ክላንሽኮቭ ጠብመንጃዎች፣ 18 ሽጉጦችና የተለያዩ ኋላቀር የጦር መሳሪያዎች 1ሺህ ከሚጠጉ መሰል ተተኳሽ ጥይቶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አመልክተዋል።
“ስለ ውያኔና ሸኔ ድርጊት ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል፤ አሸባሪዎቹን ለመደምሰስ እየተካሄደ ባለው ትግል ለመሳተፍ ከ19ሺህ በላይ የከተማዋ ወጣቶችና ሴቶች በራሳቸው ተነሳሽነት ወታዳራዊ ስልጠና ወስደው የአካባቢውን ሰላም ከማስፈን ባለፈ ግንባር ድረስ ለመዝመት በዝግጅት ላይ ናቸው ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.