Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ጉጂ ዞን ስምንት የሸኔ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ጉጂ ዞን ስምንት የሸኔ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ።
በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ከሰጡ የሸኔ አባላት መካከል አራቱ ከነትጥቃቸው እንደሆነ ኢዜአ ከስፍራው አረጋግጧል።
በአሸባሪው ሸኔ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመታለል ከቡድኑ ጋር ተቀላቅለው የነበሩ ሰዎች የቡድኑ ዓላማ አገር ማፍረስ መሆኑን በመገንዘብ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጥተዋል።
በተለይም ቡድኑ ከአሸባሪው ህወሃት ጋር አገር የማፍረስ ሴራ ነድፎ በመንቀሳቀሱ በአመራርነት ደረጃ የሚገኙ አባላቱ ጭምር በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠት መጀመራቸው ይታወቃል።
የደቡብ ዞን የሸኔ ታጣቂዎች ዋና አዛዥ አቶ ጎሌቻ ዴኒጌ በመስከረም ወር ላይ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸው ይታወሳል።
አቶ ጎሌቻ ከ14 ዓመት በላይ በደቡብ ዞን ግንባር የሸኔ ታጣቂዎችን ሲመሩ የነበሩ ሲሆን የትጥቅ ትግል ትተዉ ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነትና እኩልነት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተፈጠረው የዴሞክራሲና የሰላም አማራጭ ለመታገል ወስነዉ ተቀላቅለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.