Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት የተፈናቀሉ ወገኖችን ሁሉም እንዲደግፍ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የተፈናቀሉ ወገኖችን ሁሉም እንዲደግፍ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀንበር ጥሪ አቀረቡ፡፡
ትህነግ በአማራ ሕዝብ ላይ በፈጸመው ወረራ ከፍተኛ ግፍ መድረሱን ጠቅሰው፥ ይህንን ወራሪ ሕዝቡ ሆ ብሎ በመነሳትና በመደምሰስ የአባቶችን ታሪክ መድገም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
“ወረራውን መቀልበስና ጠላትን መደምሰስ ካልተቻለ እንደ አማራ ሕዝብ ክብራችንን አስጠብቀን መኖር አንችልም” ነው ያሉት፡፡
ክብርንና ማንነትን ለማስቀጠል በግንባር የሚደረገውን ትግል የሚያግዝ የሎጅስቲክስ ድጋፍ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡
የታጠቀ ኃይል ለመፍጠርና ለማዋጋት ከፍተኛ ሃብት እንደሚጠይቅም ጠቁመው፥ የተሰበሰበው ሀብት ለተፈለገው አገልግሎት በፍጥነት ወደ ግንባር እየተላከ የወገን ጦርን አቅም እንዲገነባ ጥረት ይደረጋልም ብለዋል።
አሁን ላይ ያለው የተፈናቃይ ወገኖች ቁጥር በርካታ በመሆኑ በቂ ድጋፍ እንዳልደረሳቸውም አንስተዋል።
የታጠቀው ኃይል፣ ወጣቶች ወደ ግንባር በመሄድ፣ ባለሀብቶች ሀብት በማሰባሰብ እና ደጀኑ ሕዝብ ስንቅ ከማቀበል ባለፈ ወደ ግንባር የሚሄዱ ዘማች ቤተሰቦችን መንከባከብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ጦርነቱ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person
0
People reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.