Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያን ለህወሓት የሚያደርጉት ድጋፍ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነው – ዶክተር አልማው ክፍሌ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያን ለአሸባሪው ሕወሓት በሳተላይት እያደረጉት ያለው ድጋፍ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነው ሲሉ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሕግና የታሪክ መምህር የሆኑት ዶክተር አልማው ክፍሌ ገለፁ።
ዶክተር አልማው በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፥ አሁን ላይ አገራችን ከአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ጋር እያደረገች ባለችው የህልውና ዘመቻ ላይ ምዕራባውያን በሳተላይት የተደገፈ እርዳታ በመስጠት ላይ ሲሆኑ ለአሸባሪ ቡድኑ የሚያደርጉት ድጋፍ አሁን የተጀመረ ሳይሆን የቆየ ነው ብለዋል።
ምዕራባውያን ኢትዮጵያን ማዳከም አፍሪካን ማዳከም ነው ብለው ከማሰባቸውና በእነርሱ መርሐ ግብር መሠረት የሚጓዝ መንግሥት ለመፍጠር ካላቸው ትልም ጋር ተያይዞ ፥ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በመጋፋት አሸባሪው ሕወሓት እንዲያንሠራራና አገር የማፍረስ እንቅስቃሴውን ገፍቶ እንዲቀጥልበት እየረዱት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
አያይዘውም ኢትዮጵያ የአፍሪካን የነፃነት ብርሃን የለኮሰችና አፍሪካውያን ስለነፃነታቸውና አንድነታቸው የሚተነፍሱባት ሳንባ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ጥርስ የነከሱባትና አገራችንንም አዘቅት ውስጥ ሊከቷት ቆርጠው መነሳታቸውን ለሽብር ቡድኑ ከሚያደርጉት ድጋፍ ተነስተን ማወቅ እንችላለን ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person
0
People reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.