Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሊያ በሶማሌ ክልል የጤና ተቋማት አገልግሎት አሠጣጥን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሶማሌ ክልል የሚገኙ የጤና ተቋማት አገልግሎት አሠጣጥ ሁኔታን እየጎበኙ ነው።
 
ሚኒስትሯ በፋፍን ዞን አውበሬ ወረዳ የአውበሬ ጤና ጽህፈት ቤት ተገኝተው በጤናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎችን ተመልክተዋል።
በጉብኝቱም የጤና ጽህፈት ቤቱ የ2013 ዓ.ም ስራ አፈጻጸምን በተመለከተ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
 
በጉብኝቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ሳህረላህ አብድላሂን ጨምሮ በጤናው ዘርፍ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
በአፈወርቅ አለሙ እና ፈቲያ አብደላ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.