Fana: At a Speed of Life!

በፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር ወንድም ስም ከተቀመጠ ገንዘብ ለማውጣት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሓት ቡድኑ አባል በፈትለወርቅ ገብረእግዚያብሔር ወንድም ስም በባንክ ከተቀመጠ ገንዘብ 267 ሚሊየን ብር ለማውጣት የሞከሩ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
 
በወንጀሉ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች ውስጥ 2 ዳኞች መሆናቸው ተገልጿል።
 
በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የፋይናስ እና ንግድ ነክ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አበበ በሰጡት መግለጫ÷ ወንጀሉ የተፈፀመው በህግ ባለሙያዎች ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ነው።
 
የሽብር ቡድኑ አባል ፈትለወርቅ ገብረእግዚያብሔር ወንድም ዳዊት ገብረእግዚያብሔር በሀሰተኛ ስሙ ቱሉ በዳዳ(ቶፊቅ ሙላት አበራ) በስራ ግንኙነት እዳ አንዳለበት በመስማማት ሀሰተኛ ሰነድ በህግ ባለሙያዎች በማዘጋጀት ፍርድ ቤት ለግልግል ዳኝት ጠይቀዋል።
 
በሀሰተኛ መንገድ በተዘጋጀውን የግልግል ፍርድ ተጠርጣሪዎቹ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ትዕዛዝ እንዲሰጣቸው ሐምሌ 16 ቀን 2013 መጠየቃቸው በመግለጫው ተነስቷል።
 
ዳኞቹ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በነበራቸው የጥቅም መመሳጠር የፍርድ ባለእዳ ዳዊት ገብረእግዚአብሄር ባልቀረበበት፤
ተጠርጣሪዎቹለፍርድ ባለመብት በሀሰተኛ ስሙ ቱሉ በዳዳ (ቶፊቅ ሙላት አበራ ) እና ጉዳይ አሰፈፃሚ ግብረ አበሮች እና በዜናዊ ወርቅነህ ገንዘብ አቅራቢነት 400 ሺህ ብር ለቅድመ ስራው ጉቦ በመስጠት አፈፃፃም እንዲወጣ አድረገዋል።
 
ሁለቱ ዳኞችም የፍርድ ባለእዳው ባልቀረበበት ትዕዛዝ እንደማይሰጥ እያወቁ ከተጠሪጣሪዎች ጋር ባላቸው የጥቅም መመሳጠር ለፍርድ ባለመብት ሆኖ ለቀረበው በሀሰተኛ ስሙ ቱሉ በዳዳ(ቶፊቅ ሙላት አበራ) 267 ሚሊየን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጪ ሆኖ በቡና ባንክ ገቢ እንዲደረግ ውሳኔ ሰጥተዋል።
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በገንዘቡ ግብይት ጥያለውን ጥርጣሬ ለፋይናስ ደንህነት አገልግሎት በሰጠው ጥቆማ ወጪ የሚደረገው 267 ሚሊየን ብር ታግዶ እንዲቆይ በማድረግ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ምርመራ ሲደረግ መቆየጡ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
 
በዚህም ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጪ ተደርጎ ለጊዜው ስሙ ባልተጠቀሰው ቡና ባንክ ቅርንጫፍ ስራ አሰኪያጅ በመሆኑ እና አስቴር ኪሮስ በተባለች የቤት ሰራተኛው የወር ደሞዟን ባንክ አስቀምጥልሻለው በሚል የባንክ ደብተር በመክፈት እና ቢሮ በማስቀመጥ ገንዘቡ ወደ ሰራተኛው ደብተር ገቢ ሳይሆን በአየር ላይ ቱሉ እስቀምጥልሻለው ብሎ ቡክ በማስከፈት፤ገንዘቡ ወደ ባንኩ ሳይገባ የስራ ሃላፊነቱን ተጠቅሞ ለተጠርጣሪው በሀሰተኛ ስሙ ቱሉ በዳዳ ለመስጠት መዘጋጀቱም ተገልጿል።
 
በተደረገው ረጅም ጊዜ የፈጀ ምርመራ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 13 ግለሰቦች ተጠርጣረው 10 በቁጥጥር ስው ማዋል መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
 
ውሳኔውን ያስተላለፉ ዳኞች የመጀመሪያው ጉዳይ ለማስፈጻም 400 ሺብር የተቀበሉ ሲሆን÷ ገንዘቡ ከወጣ ተጨማሪ የሚከፈላቸው በ3 የተለያዩ ቼኮች የተጻፉ 2 ሚሊየን ብር ፣ 3 ሚሊየን ብር እና የ5 ሚሊየን ብር ደረቅ ቼክም በቁጥጥር ስር ውሏል።
 
የዳዊት ገብረእግዚያብሄር ህጋዊ ተወካይ ረቂቅ ዜናዊ ትዕዛዝ በመቀበል ከዳሽን ባንክ 650 ሺህብር ወጪ በማድረግ ከግብረ አብሮቿ ጋር ታስፈፅም የነበረ ዜናዊ ወርቅነህ በቁጥጥር ስር መዋሏም ታውቋል።
 
የአሸባሪው ቡድን አባል ፈተለወርቅ ገብረእግዚያብሄር የፋይናስ ደንህነት አገልግሎት ማዕከል ምክትል ዳሬክተር ሆና ስታገለግል፤ ወንድሟ ዳዊት ገብረእግዚያብሄር ከ276 ሚሊየን ብር ምንም አይነት ምርመራ ሳይደረግ እንዲያወጣ ስለማድረጋቸው በመግለጫው ተነስቷል።
 
በረቀቀ መንገድ የተፈጸመው የሙስና ወንጀል በጊዜ ተደርሶበት ባይያዝ ኖሮ ለሽብር ቡድኑ የጥፋት ማስፈጸሚያ በመዋል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትል ይችል እንደነበር ተጠቁሟል።
 
አሁን ላይም ጉዳዩ ምርመራው ተጠናቆ ለአቃቤ ህግ በጉዳዩን ላይ ክስ እንዲመሰርት ተላልፏል።
 
በበላይ ተስፋዬ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.