Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የተቋቋመው የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው::
መድረኩ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራ ሲሆን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሁሉም ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል የበላይ አመራሮች ተገኝተዋል።
የግንኙነት መድረኩ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ በዝርዝር ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአብክመ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኘነት መድረክ የኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ስርአትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት የተቋቋመ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.