Fana: At a Speed of Life!

የስኳር ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ከ42 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኳር ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ለአገር መከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን 42 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወዩ ሮባ ፥ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጀነራል አስረሰ አያሌው አስረክበዋል፡፡
የተደረገው 42 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች የለገሱት የአንድ ወር ደመወዛቸው መሆኑን አቶ ወዩ ገልጸዋል።
የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች በቀጣይም ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለሰራዊቱ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ብለዋል።
የመከላከያ ሰራዊት ድጋፋ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጀነራል አስረሰ አያሌው፥ የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።
አያይዘውም ከምንም ነገር በፊት ሀገር ይቀድማል ብለው ከመከላከያ ጎን የቆሙ ተቋማት እና ግለሰቦች ክብር ይገባቸዋል ነው ያሉት።
የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነን ጨምሮ ሌሎች የሰራዊቱ መኮንኖችና የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 2 people
0
People reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.