Fana: At a Speed of Life!

ለሀገራችን አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን-የብላቴ ኮማንዶ ሰልጣኞች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀገራችን አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈልና ሀገርን ለማዳን መዘጋጀታቸውን በብላቴ ልዩ ዘመቻዎች ሃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ያሉ የኮማንዶ ሰልጣኞች ገለጹ፡፡
 
ሰልጣኞቹ ሀገር ለመበተንና ሰላሟን ለመንሳት በቁማቸው እየቃዡ ላሉ የሽብርተኛ ቡድኖች ቀብራቸውን ለማፋጠን መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።
ለብዙ ዓመት አቅፋና ደግፋ ትልቅ ደረጃ ላደረሰችን ሀገራችን ውለታዋን የምንከፍልበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ ገለጸዋል ።
የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ተወካይ ሻለቃ አበባው ሞላ÷የሀገር መወረር ያንገበገባቸው ከሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ የህልውና ዘመቻውን ለመቀላቀል በማዕከላችን ስልጠናቸውን እየወሰዱ የሚገኙ የ36ኛ እና የ37ኛ ዙር ኮማንዶ ሰልጣኞች፣ ስልጠናቸውን በእልህ ፣ በወኔ እና በቁርጠኝነት እየሰለጠኑ ይገኛሉ ብለዋል ፡፡
አሁን ላይ ያጋጠመንን ወራሪ ሃይል ለመመከት ብቻ ሳይሆን ዓለም የደረሰበትን የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ የአሰላለፍ ሚዛንን ያማከለ ስልጠናን በብቃትና በጥራት እየሰጠን እንገኛለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.