Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የንፋስ ኃይል ማመንጫ በባህር ዳርቻዎቿ ላይ እየገነባች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ የካርበን ልቀት መጠኗን ለመቀነስ የሚያስችላትን የንፋስ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖች በባህር ዳርቻዎቿ ላይ እየገነባች መሆኑን አስታወቀች፡፡
 
በዚህም በቢጫ ባህር በ40 ኪሎ ሜትር ርዝመት 150 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖችን እየገነባች ትገኛለች።
 
ይህም ለ1 ሚሊየን አባዎራዎች ዓመታዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታነት ይውላል ነው የተባለው፡፡
 
በሩዶንግ ባህር ዳርቻ በ12 ቢሊየን ዩዋን የተገነባው የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን በሀገሪቱ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ተጠቁሟል፡፡
 
የቻይና የኃይል አስተዳደር እንዳስታወቀው ÷ በፈረንጆቹ 2025 ሀገሪቱ ከድንጋይ ከሰል የምታመነጨውን ኃይል ለመቀነስና ከንፋስ እና ከፀሃይ ኃይል የምታመነጨውን ኃይል ወደ 16 ነጥብ 5 በመቶ ለማሳደግ አቅዳለች፡፡
 
ቻይና በፈረንጆቹ 2030 ሃያ አምስት በመቶ የሚሆነውን የኃይል አቅርቦት ከካርበን ልቀት ነፃ ከሆኑ የኃይል አማራጮች ለማግኘት እና በፈረንጆቹ 2005 ከተመዘገበው የካርበን ልቀት መጠን አንፃር በ65 በመቶ የወረደ በካይ ጋዝ እውን ለማድረግ ማቀዷን የዘገበው ሲጂቲ ኤን ነው፡፡
 
በአሁኑ ወቅት የንፋስ ኃይል በቻይና በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኝ ታዳሽ ኃይል መሆኑ ይነገራል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.