Fana: At a Speed of Life!

ህንድና ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድና ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሁለቱ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ገልጸዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒትሮች ይህን ያሉት÷ አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማቸውን ደስታ በገለፁበት ወቅት ነው።

የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ሱብራማንያ ጄይሻንካር÷ ኢትዮጵያ እና ህንድ በመካከላቸው ያለውን አቅም ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ለሁለቱ ሀገራት ዜጎች ይበልጥ ተጠቃሚነት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

የጣሊያኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲ ማዮ በበኩላቸው÷ የኢጣሊያን እና ኢትዮጵያ ግንኙነት ታሪካዊ እና ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረ መሆኑን በመጠቆም÷ ይኸው ታሪካዊ ግንኙነታቸውም በቀጣይ ወደ ተሻለ ደረጃ መሸጋገር እንደሚገባው አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት ቁልፍ አገር በመሆኗ አሁን ላይ በውስጧ ያጋጠማትን ፈተና ለማለፍ እያደረገችው ያለውን ጥረት ጣሊያን ትደግፋለች ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.