Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት ዝርፊያ ምክንያት ለተፈናቃዮች እርዳታ ማቅረብ አልተቻለም

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በእርዳታ መጋዘኖች ላይ በፈፀመው ዝርፊያና ትራንስፖርት ችግር ምክንያት ለሁሉም ተፈናቃይ ወገኖች በቂ እርዳታን ማቅረብ እንዳልተቻለ ተገለፀ፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ ንፁሃን ከአፋር ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዋል።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የጋዜጠኞች ቡድን ከሰሞኑ አሸባሪ ቡድኑ ሰርጎ ከገባባቸው ጭፍራና እዋ አካባቢዎች ተፈናቅለው የመጡ ዜጎች በተጠለሉበት የኢባይ ዋኢዳል ጊዜያዊ መጠለያ ጉብኝት አድርጓል።

በስፍራው የመጠለያ ችግር መኖሩን፣ በቂ ድጋፍም እያገኙ አለመሆኑን ተፈናቃዮቹ አንስተዋል፡፡

በአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የአደጋ መከላከልና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ኤክስፐርት መሀመድ አብደላ÷ ችግሩ የተፈጠረው አሸባሪ ቡድኑ በጭፍራ ይገኝ የነበረን የእርዳታ ማዕከል በመውረሩ፣ በትራንስፖርት እጥረትና የተፈናቃዮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ እንደሆነ አስረድተዋል።

በኢባይ ዋኢዳል ጊዜያዊ መጠለያ 23 ሺህ የሚደርሱ ዜጎች የሚገኙ ሲሆን÷15 በመቶ ያህሉ ህፃናትና ነብሰጡር እናቶች ናቸው።

ሆኖም ለህፃናቱ የሚያስፈልገውን አልሚ ምግብ ማድረስ አልተቻለም፤ለአዋቂዎችም ቢሆን በነፍስ ወከፍ ለአንድ ቤተሰብ ከሚያስፈልገው መጠን ያነሰ ነው የሚቀርበው ብለዋል።

አቶ መሀመድ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመጭዎቹ ሶስት ቀናት እንደሚሰራ ገልፀው የተራድኦ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በጊዜያዊ መጠላያው በአሁኑ ጊዜ 2ሺህ 500 አባወራዎች ድጋፍ ያገኙ ሲሆን ቀሪ 2 ሺህ ያህል አባወራዎች ግን ድጋፍ አላገኙም።

በአፈወርቅ እያዩና በፀጋዬ ወንደወሰን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.