Fana: At a Speed of Life!

አቶ ታገሰ ጫፎ በኢትዮጵያ ከሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ በኢትዮጵያ ከሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጃማል አብዱላህ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው ሁለቱ አገሮች የቆየና ረጀም ታሪክ ያላቸው በመሆኑ በሁለተናዊ ዘርፎች በትብብር በመስራት የዲፕሎማሲውን ስራ ማስቀጥል እንደሚገባ አፈ-ጉባኤው ጠቁመዋል፡፡

የሁለቱን አገሮች ግንኙነት በማቀራረብ የፓርላማ የወዳጅነት ግንኙነትን፤ የህዝብ ለህዝብ እና የንግዱን ማህበረሰብ በማጠናከር በትብብር እንደሚሰሩ በውይይታቸው አንስተው ሳውዲ አረቢያ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚበረታታ በመሆኑ ይህንኑ ግንኙነት በማጠናከር የህዝቦችን ኢኮኒሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡

አምባሳደር ሳሚ ጃማል በበኩላቸው÷ ሁለቱ አገሮች ጠንካራና ታሪካዊ የሆነ ትስስር ያላቸው መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነት ለማጠናከር ተቀራርበው እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.