Fana: At a Speed of Life!

የጀርመን ኩባንያዎችን በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ያለመ የምክክር መድረክ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን ግዙፍ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በስፋት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ያለመ የምክክር መድረክ በበይነመረብ ተካሂዷል።

የምክክር መድረኩን የጀርመን- አፍሪካ የቢዝነስ ማህበር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ከ50 በላይ የጀርመን ካምፓኒዎች ተሳትፈውበታል።

በምክክር መድረኩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጀርመን ረጅም ዘመን የተሻጋረ ወዳጅነት ከኢትዮያ ጋር እንዳለት አስታውሰው፣ ግንኙነቱን በቢዝነስና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የበለጠ ማስፋትና ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

የጀርመን መንግስት ባለሀብቶች አፍሪካ ላይ መዋለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚያደረገውን ማበረታታት የሚደነቅ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በቀጣይም ኩባንያዎች በኢትዮጰያ መዋለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ሁኔታዎች እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል።

አምባሳደር ሬድዋን በንግግራቸውም ከጀርመን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ኩባንያዎች ያለምንም እንግልት ምቹ አገልግሎት እንደሚያገኙ ያሳወቁ ሲሆን የተሻለ ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉበትን የኢንቨስትመንት ዘርፎችንም ጠቁመዋቸዋል።

መንግስት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የፖሊሲ ማሻሻያና ሌሎችንም ምቹ ሁኔታዎች እንደፈጠረ መጥቀሳቸውን ከውይጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጀርመን አፍሪካ ቢዝነስ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ክላውዲያ ቮስ በበኩላቸው የጀርመን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያለውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በስፋት መዋለ ንዋያቸውን እንደሚያፈሱ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.