Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር መቅደስ ዳባ የሕክምና ሽልማትን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶክተር መቅደስ ዳባ በማኅጸንና ጽንስ ሕክምና ባደረጉት ምርምርና አስተዋጽዖ በሴቶች ዘርፍ የዓለም የጽንስና ማኅፀን ሕክምና ሽልማትን አሸነፉ።

የዓለም የጽንስና ማህጸን ሕክምና ፌዴሬሽን በጽንስና ማኅጸን ሕክምና በዓለም ዓቀፍ እንዲሁም በሀገር ደረጃ እ.አ.አ በ2021 በላቀ ሁኔታ አስተዋጽኦ ያደረጉ የዘርፉ ሴት ሃኪሞችን ይፋ አድርጓል።

በሽልማቱ በእናቶች፣ በሴቶች እና ልጆች ጤና ላበረከቱ ሴት የዘርፉ ሃኪሞችም እውቅና እንደሚሰጥ ተነግሯል።

ዶክተር መቅደስ ዳባም በማኅጸንና ጽንስ ሕክምና ባደረጉት ምርምርና አስተዋጽዖ የዓለም የጽንስና ማኅፀን የሴቶች ዘርፍ ሽልማትን ማሸነፋቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.