Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡ ከሀሰተኛ መረጃዎች እራሱን እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ ያልተረጋገጡ መረጃዎችና በአንዳንድ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ተቋማት ስም ሆን ተብሎ ከሚተላለፉ ሃሰተኛ መረጃዎች እራሱን መጠበቅ እንደሚገባው ማሳሰቢያ ተሰጠ።

በሀገሪቱ መረጋጋት እንዳይኖርና በየአካባቢው ያለው ህብረተሰብ እንዲሸበር የጥፋት ኃይሎች በመንግስት ኃላፊዎችና በተቋማት ስም የተሳሳቱ መረጃዎችን ማስተላለፍ የዕለት ከዕለት ተግባራቸው ማድረጋቸውም ተጠቁሟል።

ህብረተሰቡ ይሄን በመረዳት የማንኛውንም መረጃ ትክክለኛነት ሳያረጋግጥ እና ከትክክለኛ ምንጭ ሳያጣራ መረጃዎቹን ከማሰራጨት መቆጠብ እና በመረጃው መረበሽ እንደሌለበት የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታውቋል።

የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጠው ማሳሰቢያ ÷ በቀድሞው ፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊና አሁን ላይ የሠላም ሚኒስትር በሆኑት በአቶ ብናልፍ አንዷለም ስም ሀሰተኛ መረጃ የተሰራጨ ሲሆን፥ ሚኒስትሩ የፌስ ቡክ ገጽም ሆነ ሌላ የማህበራዊ ሚዲያ የግል አካውንት የሌላቸው መሆኑን የኢዜአ መረጃ ያመለክታል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ በመንግስት ኃላፊዎችና በተቋማት ስም ከሚተላለፉ ሃሰተኛ መረጃዎች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.