Fana: At a Speed of Life!

ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር የጠላትን ሴራ ማክሸፍ ይገባል -ብርጋዴር ጀኔራል ናስር አባዲጋ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድኑ የሚነዛውን የሃሰት ወሬ ባለመስማት ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር የጠላትን ሴራ ማክሸፍ እንደሚገባ ብርጋዴር ጀኔራል ናስር አባዲጋ ተናገሩ።

ቡድኑ ከሀገር ማፍረስ ተግባሩ በሻገር ልዩነትን በመፍጠር ዜጎችን እርስ በርስ ማጋጨት ሌላው ያደገበት ስልቱ መሆኑም ተመላክቷል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ ዛሬ የህዝብ ለህዝብ መድረክ በተካሄደበት ወቅት፥ በመከላከያ ሠራዊት የስምንተኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ናስር አባዲጋ እንዳሉት፥ አሸባሪው ህወሃት በስልጣን ዘመኑም ይሁን አሁን ግጭት ቀስቃሽና አገር አውዳሚ ተግባራትን ሆን ብሎ እየፈጸመ ነው።

የሽብር ተግባሩን በግልጽ ከጀመረ ወዲህም በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ካደረሰው ጉዳት ባለፈ ልዩነቶችን በመፍጠር ዜጎችን እርስ በርስ ለማጋጨት እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

“ብሔርና ሃይማኖት የግጭት መንስኤ ሊሆን አይገባም” ያሉት ዋና አዛዡ፤ “አሸባሪ ቡድኑ በሚነዛው የሃሰት ፕሮፖጋንዳና የጥላቻ ወሬ ተጠልፎ ከመውደቅ ይልቅ ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር የጠላትን ሴራ ማክሸፍ ይገባል” ብለዋል።

ህዝቡ ወንድማማችነትን በማጠናከር ለህግ የበላይነትነና ለሰላም መከበር የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ብርጋዴር ጄነራሉ ጠይቀዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የምዕራብ ጎንደር ዞን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቢክስ ወርቄ በበኩላቸው፥ የዞኑ ህዝብ ህብረቱን በማጠናከር ሀገሪቱን ከገጠማት ፈተና ለማውጣት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለበት አመልክተዋል።

በዞኑ የሚታየውን ህገወጥ እንቅስቃሴ ለማስቆም ቁርጠኛ ሆኖ መስራት ይገባል ያሉት ደግሞ የገንዳ ውሃ ከተማ ነዋሪ የሀገር ሽማግሌ አቶ ገንዘብ ጀምበር ናቸው።

በመድረኩ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ አካላት፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ሃላፊዎች መገኛታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.