Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ጎጃም ዞን በመስኖ የለማ የአቮካዶ ልማት ፕሮጀክት እየተጎበኘ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ በቆጋ መስኖ ፕሮጀክት የለማ የአቮካዶ እና የተለያዩ ሰብሎች ጉብኝት እየተካሄደ ነው።
የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅአቶ አቢዮት ብሩ ፥ በፕሮጀክቱ አጠቃላይ 6 ሺህ 512 ሄክታር መሬትእየለማ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህም ውስጥ በአቮካዶ 260 ሄክታር መሬት መልማቱን ጠቁመው፥ በ10 ቀበሌዎች በ12 ክላስተር እየለማ ባለው አቮካዶ 845 አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስተዋል።
የአቮካዶ ምርት ወደ ውጭ ከ 2011 ጀምሮ እየተላከ መሆኑን ገልጸው፥ በ2011 ዓ.ም 90 ኩንታል በ2012 ዓ.ም 750 ኩንታል እንዲሁም በ2013 ዓ.ም 1 ሺህ 652 ኩንታል መላኩን አብራርተዋል።
በአቮካዶ ልማት ተሳታፊ ከሆኑት አርሶ አደሮች አርሶ አደር ደረብ አበይ እና አርሶአደር መለሰ አይሸሽም አቮካዶ በማልማት የተሻለ ጥቅም ስለማግኘታቸው ገልጸዋል።
በጉብኝቱ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በሰላም አስመላሽ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.