Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ66ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከአራት ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።
ዩኒቨርስቲው በ 2013 ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎችና ፕሮግራሞች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በድህረ ምረቃ፣ በዶክትሬት ዲግሪ እና በስፔሻሊቲ ያሰለጠናቸውን ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ ያለው።
በዩኒቨርስቲው የመማክርት ጉባኤ ፀድቆላቸው ለምረቃ የበቁት ተማሪዎች በመደበኛ፣ በተከታታይ ፣ በርቀትና በክረምት የትምህርት መርሃ ግብዎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን  አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ66ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከአራት ሺህ በላይ ተማሪዎችን  አስመርቋል ።

ዩኒቨርስቲው በ 2013 ከተለያዩ  የትምህርት ክፍሎችና ፕሮግራሞች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በድህረ ምረቃ፣ በዶክትሬት ዲግሪ እና በስፔሻሊቲ  ያሰለጠናቸውን  ከ4  ሺህ በላይ ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።

በዩኒቨርስቲው የመማክርት ጉባኤ  ፀድቆላቸው  ለምረቃ የበቁት ተማሪዎች በመደበኛ፣ በተከታታይ ፣ በርቀትና በክረምት የትምህርት መርሃ ግብሮች ከ200 በላይ በሚሆኑ የትምህርት ክፍሎች  ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዶክትሬት ዲግሪ 28 ፣ በድህረ ምረቃ 383 ፣ በጤና ስፔሻሊቲ 18 እንዲሁም በቅድመ ምረቃ ከ 3ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ከ 1ሺህ 200 በላይ የሚሆኑት ተመራቂዎች ሴቶች እንደሆኑ ተገልጿል።

ዶክተር  ጀማል ዩሱፍ የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ÷ ዩቨርስቲው ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ከመማር ማስተማር በተጨማሪ የማህበረሰብ ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምሮችን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በ 2013 ዓ.ም 85 የምርምሮ ሥራዎች መጠናቀቃቸውን 280 የሚሆኑ ደግሞ በሂደት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም 27 የቴክኖሎጂ ውጤቶች በማውጣት  ለ 45 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች ክፍሎች እንዲደርሱ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

በምረቃ ስነ ስርአቱ  ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌድሪ የሰራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት ÷አሁን እንደ ሀገር ያጋጠመን ችግር የበለጠ አንድነታችንን የሚያጠናክር በመሆኑ በተማርነው መስክ ያገኘነውን እውቀት ወደ ተግባር ለመቀየር የምንጥር ከሆነ ሃገራችን ኢትዮጵያ ወደፊት ለማሻገር ያስቸላል ካሉ በኋላ ወደ ስራው ዓለም በምትቀላቀሉበት ጊዜ ህዝብ በቅንነት እንድታገለግሉ ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በዩኒቨርስቲው የስፖርት ሳይንስ አካዳሚ በተካሄደው የምረቃ ሥነ-ስርአት በትምርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች ዲግሪ እና የተለያዩ ሽልማቶችን ከወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል እና ከሌሎች እንግዶች እጅ ተቀብለዋል።

የሐረማያ ዩንቨርስቲ የመማር ማስተማሩን ከጀመረበት ከ1946 ዓ.ም ጀምሮ ከ110 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የሙያ መስኮች  አሰልጥኖ ለሃገሪቱ ልማት መፍጠን የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት የቻለ አንጋፋ የትምህርት ተቌም  ነው፡ ፡

በተሾመ ኃይሉ

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግ

61,694
People reached
1,959
Engagements
Boost Post
925
18 Comments
21 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.