Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ቡድን ለሁለት አመት የሚሆን ቀለብ ከአማራ ክልል እንሰበስባለን ብሎ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት አመት የሚሆን ቀለብ ከአማራ ክልል እንሰበስባለን ብሎ አሸባሪው ቡድን አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡

ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጠው አገልግሎቱ አሸባሪው ቡድን ላለፉት ተከታታይ ቀናት ከፍተኛ መንጋ በማሰለፍ ጥቃት በመፈፀም የእህል ዘረፋ አድርጓል ብሏል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በመንጋ የመጣው ሃይል ሙትና ቁስለኛ እየሆነ በመከላከያውና በሌሎች ፀጥታ ሃይል እየተደመሰሰ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳው ህወሓት ባለፉት ቀናት ከፍተኛ የመንጋ ሃይል በማሰለፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን መግደሉን እና ሴቶችን በአስነዋሪ ሁኔታ መድፈሩን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

አሸባሪው ቡድን አሁን እያደረገው ያለው ነገር ቢኖር የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት ህዝቡን ማሸበር ነው ሲሉም ይህን ለማሳካት ከውስጥ ባንዳዎችን እየተጠቀመ እንዳለም ገልፀዋል፡፡

አሁን ሀገሪቱ እየተፋለመች ያለችው ሁለት ግንባር መሆኑን ህዝቡ ማወቅ አለበት ያሉት ሚኒስትሩ ፥ እሱም ወታደራዊ ግንባር እና ኢኮኖሚያዊ ግንባር ነው ብለዋል፡፡

ስለዚህም በሁለቱም ድል ለማምጣት ህዝቡ  ከዚህ ቀደሙ በበለጠ መጠንከር ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡

በወታደራዊ ግንባር ከሚደረገው ትግል ባለፈ በኢኮኖሚው ግንባር ውጤት ለማምጣት ከውጭ የተቃጡ ጫናዎችን ለመሻገር ህዝቡ በያለበት ዘርፍ ጠንክሮ መስራት አስፈላጊ እንደሆነም አሳስበዋል፡፡

በህዝብ ማዕበል ሀገር ለማተራመስ የተነሳውን ሃይልም ባጭር ጊዜ ለመቋጨት በህዝብ ማዕበል መመከት ስለሚያስፈልግ ሁሉም እራሱን እንዲያዘጋጅም ጥሪ ቀርቧል፡፡

አሸባሪው ቡድን ከ12 ዓመት እስከ 65ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ህፃናትን፣አዛውንቶችን፣ነብሰጡሮችን በጦርነቱ እየማገዳቸው እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ሀገር ሰላም እንድትሆን ይህ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰስ እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.