Fana: At a Speed of Life!

ከ52 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመትየኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግምታዊ ዋጋዉ 52 ሚሊየን 607 ሺህ 221 ብር የሚሆን የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙን የኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።
ባሳለፍነው ሳምንት የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችበጉምሩክ ኮሚሽን በ13 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና የፍተሻ ኬላዎች ላይ ሲሆን ፥ወደ መሀል አገር በህገ ወጥ መንገድ ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ እና ከሀገር ዉጪ ለማዉጣት ሲሞክሩ የተያዙ መሆናቸው ተገልጿል።
ወደ መሀል ሀገር በህገወጥ መንገድ ለማስገባት ሲሞክሩ የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል የኤሌክትሮንክስ እቃዎች፤ ኮስሞቲክስ፤ ልባሽ ጨርቆች፤ መለዋወጫዎች፣ ምግብ ነክ እና መድሃኒቶች የሚገኙበት ሲሆን፥ 48 ሚሊየን 717 ሺህ 996 ብር የሚያወጡ መሆናቸው ተመላክቷል።
በሌላም በኩል ወደ ዉጪ ሀገር 3 ሚሊየን 889 ሺህ 225 ብር የሚሆን የውጭ ምንዛሬ የአሜሪካ ዶላር፣ ዩሮ፣ ፓዎንድ፣ የሳውዲ ሪያል፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ድርሃም  በህገ ወጥ መንገድ ሊወጣ ሲል መመያዙን ከኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.