Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን ከአጎዋ ለማስወጣት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያጤነው ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያን በአጎዋ የምታገኛቸውን ጥቅሞች ለማሳጣት እና ከአባልነት እንድትወጣ ለማድረግ የጀመረውን እንቅስቃሴ በድጋሜ እንዲያጤነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በይፋዊ ደብዳቤ ጠይቋል፡፡
ኢትዮጵያ ከብዙ የበለጸጉ ሀገራት ግንባር ቀደም አለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖችን እንድትስብ የአጎዋ ኢኒሼቲቭ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ደብዳቤው አመላክቷል፡፡
ከነዚህም መካከል የዩኤስ ግዙፉ ፒቪኤች – የካልቪን ክላይን ፣ ቫን ሄውሰን፣ ኢዞድ፣ አርሮ፣ ስፒዶ፣ ቶሚ ሂልፊገር እና ሌሎች ዋና ዋና ብራንዶች ይጠቀሳሉ።
ስለሆነም ኢትዮጵያ የአጎዋ ዝርዝር ዉስጥ እንድትወጣ የማድረጉ ሃሳብ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የውጭ ባለሀብቶች ዘንድ ትልቅ ስጋት የሚፈጥር ነው ይላል ደብዳቤው፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በመሆኑ÷ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል በሚል ከአጎዋ የመሰረዝ እቅዱን በድጋሚ ሊመከለተው ይገባል ተብሏል፡፡
የአሜሪካ መንግስት ይህንን ማእቀብ በኢትዮጵያ ላይ ለመጣል ያነሳሳዉ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ በተለያዩ ቡድኖች በሚነሡት የተሳሳተ መረጃ ላይ የተመሠረተ ነው ብለን እናምናለን ይላል ደብዳቤው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.