Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ስንዴ ለማልማት በ2 ቢሊየን ብር ባለሀብቶች ሥራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በዱብቲ ቆላማ አካባቢ ስንዴ ለማልማት በ2 ቢሊየን ብር በጀት ባለሀብቶቸ በጋራ ሥራ መጀመራቸውን ገለጹ፡፡
የመሬት ዝግጅት፣ የሰው ሀይል እና የቁሳቁስ አቅርቦት ስራ አጠናቀው ወደ ተግባር ገብተናል ብለዋል ባለሀብቶቹ፡፡
ባለሃብቶቹ 7 ጓደኛሞች ሲሆኑ÷ የአፋር ክልል መንግስት ባለሀብቶቸ ወደ ክልሉ በመምጣት ኢንቨስት እንዲደርጉ ያቀረበውን ጥሪ ተቀብለው በመምጣት ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለሀብቱ አቶ ታጠቅ አሰፋ ለአፋር ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደገለጹት÷ በአጠቃላይ በ19 ሺህ ሄክታር ላይ ለምናከናው የልማት ስራ 2ቢሊየን ብር በጀት ተይዟል ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግስት በጥሩ ሁኔታ እንደተቀበላቸው ጠቁመው÷ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተባብረን በመስራት ከውጭ የሚመጣውን ስንዴ ለማስቀረት ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
የአውሲ ረሱ አስተዳደር አቶ አቡበከር ኢሴ እንደሀገር ብሎም እንደ ክልል በተያዘው አቅጣጫ መሰረት በዱብቲ ወረዳ አየተሰሩ ያሉት የስንዴ ልማት ባለሀብቶች እያለሙ ነው፤ እኛም ድጋፍ እያድረግን ላቸው ነው ብለዋል፡፡
የዱብቲ ወረዳ አስተዳደር አቶ አወል አብዱ÷ አሁን ላይ በ5 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ባለሀብቶቹ ስራ መጀመራቸውን ጠቁመው÷ የአካባቢው ማህበረሰብም የስራ እድል እየተፈጠረለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.