Fana: At a Speed of Life!

የአየሁ የቡና እርሻ ልማት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሄክታር ይገኝ የነበረውን 8 ኩንታል ወደ 25 ያሳድጋል- ዶ/ር ፍፁም አሰፋ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አየሁ የእርሻ ልማት ያለማው ቡና እንደሀገር በሄክታር የሚገኘውን ምርታማነት የሚያሳድግ ነው ሲሉ የፕላን ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ተናገሩ።
ሚንስትሯ ይህን ያሉት÷ በአማራ ክልል በኢትዮ አግሪ ሴፍት አየሁ የቡና እርሻ ልማት ተገኝተው የበቆሎና የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ነው።
በሀገር ደረጃ በሄክታር ከቡና በሄክታር 8 ኩንታል ቡና ነው የሚገኝው ያሉት ሚንስትሯ÷ መንግስት ይህን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በአማራ ክልል አየሁ የእርሻ ልማት አሁን የለማው ቡና የምርታማነት መጠኑ በሄክታር 25 ኩንታል ቡና እንደሚሆን ያመለከቱት ዶክተር ፍፁም÷ ይህም የተሻለ ምርታማነት ከተሰራ በዘርፉ የተሸለ ገቢ እንደሚገኝ ያሳያል ብለዋል።
የችግሮቹ መፍትሄ በአርሶአደሩ ማሳ ምልከታ በማድረግ የሚቀመጥ እንደሆነ የገለፁት ሚንስትሯ÷ መንግሥት ተገቢውን ድጋፍ እያደረገ በቀጣይ ስራዎችን በትኩረት ይመራል ነው ያሉት።
ከ620 በላይ አይነት ያላቸው የመካናይዜሽን እርሻ ልማትን ማሳለጥ የሚችሉ ዕቃዎች እንዲገቡ መንግስት ፈቃድ መስጠቱን ሚንስትሯ ገልፀዋል።
በሰላም አስመላሽ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.