Fana: At a Speed of Life!

አማኑኤል ጸጋአብ ህንጻ ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ከሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ አማኑኤል ጸጋአብ ህንጻ ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳትና ድንገተኛ አገልግሎት ባለሙያዎች ፣የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ፣ የአካባቢው ወጣቶች እና ነዋሪዎች የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር እና ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት ባደረጉት የጋራ ርብርብ አደጋው በቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረታሪ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
በቀጣይም የእሳት አደጋውን መንስኤ ፣በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አማካኝነት መረጃ ይሰጣሉ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.