Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን በታሪኳ የሞከረ እንጅ ያሽነፈ ኃይል አልነበረም፤ አይኖርምም- የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በታሪኳ የሞከረ እንጅ ያሽነፈ ኃይል አልነበረም፤አይኖርምም ሲል የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ፡፡
 
የየደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡
 
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
 
ኢትዮጵያን በታሪኳ የሞከረ እንጅ ያሽነፈ ኃይል አልነበረም፤ አይኖርምም፡፡
 
ከጽንሰ ሀሳቡ እስከ ውልደቱና እድገቱ አልፎም የኖረበትን 27 ዓመታት በሙሉ ለስልጣኑ ሲል ኢትዮጵያን በዘር፣ በኃይማኖት፣ በጎሳና በጎጥ ከፋፍሎ ስመዘብር የቆየው አሸባሪው ትህነግ ቡድን ብሶት በአገራዊ ለውጥ ምክንያት የበላይነቱን ካጣበት ጊዜ ጀምሮ “እኔ ያልመራሁት ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት” በሚል እሳቤ ኢትዮጵያውያን ለማፍረስ ያለ የሌለውን ኃይል አሰቡባስቦ እየዘመተ ይገኛል።
 
በከፍተኛ መስዋዕትነት የመጣውን አገራዊ ለውጡን ለመቀልበስ በተለያዩ ጊዜያት ሞክሮ ያልተሳካለት ይሄው አሸባሪ ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ ም የአገራችን ዳር ድንበር በመጠበቅ ላይ በነበረውን በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በመሰንዘር በይፋ ኢትዮጵያውያን በይፋ መውጋት ከጀመረ ድፍን አንድ ዓመት ሊሞላው ቀናቶች ብቻ ቀርተውታል። ዛሬም ይህንን እኩይ ተግባር ሳያቆም እየወጋት ይገኛል።
 
በሰሜን እዝ ጥቃቱ የተቆጣው መከላከያ ኃይላችንና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በወሰደው ህግ ማስከበር ዘመቻ የጥቃቱ ጠንሳሾችና ባለቤቶችን ለህግ ማቅረብ፣ እርምጃ በመውሰድና የቀሩትን መበተን ቢቻልም፣ በህግ ማስከበሩ የተጎዱ የትግራይ አከባቢዎችን መልሶ ለማቋቋምና አርሶ አደሮች እርሻቸውን ተረጋግተው እንድያርሱ የተሰጠውን ጊዜ አሸባሪ ቡድኑ እንደ መልካም አጋጣም በመጠቀም በአማራና አፋር ክልሎች ንጹሐንን በመግደል፣ ኢትዮጵያዊነትን በማዋረድና አገር የማፍረስ እኩይ ተግባሩን በድጋሜ በመፈጸም ኢትዮጵያን የማፍረስ ቀዤቱን ቀጥሎውበታል።
 
ጁንታው በፈጸማቸው በእነዚህ ጥቃቶች ንጹሃን ተገድለዋል፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤ በእናቶችና ሴት እህቶቻችን ላይ አሳዛኝና አስነዋሪ ተግባሮች ተፈጽሟል።
 
ከተቻለ ኢትዮጵያዊያንን በኃይል በማንበርከክ ወደ ቀድሞ ስልጣን መመለስ ካልሆነ ራሱ ያልመራትን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ዓልሞ የተነሳው ይኸው ቡድን የቅዠት ዓላማውን ለማስፈጸም የኢትዮጵያን አንድነትና ጥንካሬ የማይፈልጉ ታርካዊ የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎችን አስተባብሮ እየሰራ ይገኛል።
 
ታልቋ ኢትዮጵያ በታሪኳ ተፈትና እንጂ ተንበርክካ እንደማታውቅ፣ በውጭ ጠላቶችም ሆነ በውስጥ ባንዳዎች ቢሞከሩት እንጂ ተሸንፋ እንደማታውቅ ታርክ ምስክር ብቻም ሳይሆን ጠላትም ወዳጅም የማይክደው ሀቅ ነው።
 
የዚህ ዋነኛው ምስጥር ኢትዮጵያዊያን በአገር አንድነትና በሉዓላዊነት ጉዳይ ላይ ድርድር አለማወቃቸው ነው።ዛሬም እንደ ጥንቱ የአሁኑ ትውልድ ትላንት አያቶቻችንና ቅድመ አያቶቻችን በከፈሉት ህይወት መስዋዕት ያወረሱትን ነጻነት ከእጃዙር ቅኝ ገዥዎች ከውስጥ ባንዳ የመከላከልና ለመጪው ትውልድ ነጻ ሀገር የማስረከብ ኃላፊነት ተጥሎብናል።
 
ስለሆነም በአገር ሉዓላዊነት ላይ ድርድር የማያውቀውን ህዝባችን በዘር፣ በፓለቲካና በኃይማኖት ሳይለያይ አሸባሪው ህወሓት ጁንታ ቡድን አገር ለማፍረስ በያዘው እቅድ በአሁኑ ወቅት በአማራና አፋር ክልል ህዝቦች ላይ እየፈጸመ ያለውን ጥፋት በጋራ በመመከት ጁንታውን ግብዓተ መረቱን ለአንደና ለመጨረሻ ለመፈጸም በጋራ መነሳት አለብን።
 
የክልላችን ብልጽግና ፓርቲ አመራሩን፣ አባሉንና መላው የክልላችን ነዋሪዎች በማስተባበር ጀግናው አገር መከላከያ ሠራዊታችን አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በዓይነት፣ በገንዘብና በሞራል እየደገፈ የቆየ ሲሆን ይህንን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።
 
ለአገር ሠላም፣ አንድነትና ሉዓላዊነት ነቀርሳ የሆነውን ይህን የጥፈት ኃይል እስከ ወዲያኛው ተሸኝቶ የህልውና ዘመቻው በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የተጀመሩ ስራዎችን ለማሳካት የክልላችን ህዝቦች ከአገር መከላከያ ጉን እንዲቆም የክልሉ ፓርቲ ጽ/ቤት ጥሪውን ያቀርባል።
 
የክልላችን ፀጥታ ኃይሎችና ወጣቶች ክልላችን ሰላምና ደህንነት በንቃት በመከታተል የጀመሩትን ስራ እንድያጠናከሩና ፀጥታ ኃይሎች የጋራ ሰላም ለማስከበር ለሚያደርጉት ጥረት ህብረተሰቡም እንድተባብራቸውም ዬሳስባል።
 
የየደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት
 
ጥቅምት 21/2014 ዓ.ም
 
ሐዋሳ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.