Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የጸጥታ አካላት ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ የሚገኙ ሰላም አስከባሪዎች፣ ሚሊሻዎች እና ፋኖዎች በዛሬው ዕለት ወደ ግንባር ዘምተዋል።
 
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ÷አሸባሪው ህውሓት የመረጠውን ህዝባዊ ጦርነት ለመመከት ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ በአንድነት እንዲዘጋጅ አሳስበዋል።
 
እነዚህ የፀጥታ አካለት ከመከላከያ እና ከልዩ ሃይል ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለመበተን በአሸባሪ ቡድኑ የተሸረበውን ሴራ ያመክናሉ ነው ያሉት።
 
ሁሉም የአማራ ህዝብ ስንቅ ከራሴ ፤ትጥቅ ከጠላቴ በሚል መንፈስ ለህልውናው ወደ ግምባር መዝመት አለበት ሲሉም ከንቲባው ተናግረዋል።
 
ከንቲባው የክልሉ መንግስት ያቀረበውን ህዝባዊ የክተት ጥሪ በመቀበል የከተማ ነዋሪዎች ወደ ግንባር እንዲዘምቱ ለማድረግ ያለ እረፍት ይሰራል ብለዋል።
 
በዘማች የፀጥታ አካለት ሽኝት መርሃ ግብሩ የተገኙት አቶ ብርሃኑ ጣምያለው በበኩላቸው÷ ከስድስት ሚሊየን በላይ አማራዎች በአሸባሪ ብድኑ በተያዙ አካባቢዎች እንግልት ላይ መሆናቸውን በመረዳት ለመዝመት የበቃ አማራ ሁሉ ወደ ግንባር መዝመት አለበት ብለዋል።
 
መደበኛ የፀጥታ አካላት ከሚያደርጉት ተጋድሎ ጎን ለጎን ህዝባዊ ማዕበል በመፍጠር እየመጣ ያለውን ማዕበል መግታት ይገባልም ነው ያሉት።
 
ዘማች የፀጥታ አካላቱ አማራን ለማጥፋት ህውሓት የትግራይን ህዝብ እያነሳሳ መሆኑን ሀሉም አማራ በመረዳት ለህልውናው መታገል እና መዝመት አለበት ብለዋል ።
 
የትግራይ ህዝብ አሸባሪ ቡድኑ ከልጅ እስከ አዛውንት በማዝመት አማራን ለማጥፋት እያደረገ የሚገኘውን ጥረት ህዝባዊ ትብብርን እና ተጋድሎን በመፍጠር መግታት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
 
በክብረወሰን ኑሩ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.