Fana: At a Speed of Life!

በህዝብ ትግል የተገኘውን ለውጥ ለመቀልበስ በህወሓት የተቃጣውን ጥቃት ህብረተሰቡ መመከት አለበት-የኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ትግል የተገኘውን ለውጥ ለመቀልበስ በህወሓት የተቃጣውን ጥቃት ህብረተሰቡ በተቀናጀ መልኩ መመከት አንዳለበት የኦሮሚያ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡
 
የቢሮው ሃላፊ አቶ ሻፊ ሁሴን በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ÷ የሸብር ቡድኑ ህወሓት ላለፉት 27 ዓመታት የክልሉን ህዝብ በማሰቃየት ንብረቱን ያለ አግባብ ሲዘርፍ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
 
ቡድኑ በህዝብ ትግል ከተወገደ በኋላም አሁን ላይ የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስ ግልጽ ጥቃት በመክፈት የተለያዩ እንቅፋቶችን በመፍጠር ላይ ይገኛል ነው ያሉት ፡፡
 
ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ የኢትዮጵያን ሰላም አደፍርሰው የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡
 
ይህንን የጥፋት ስራም በኦሮሚያ ክልል እየሰራ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል አቶ ሻፊ በመግለጫቸው::
 
አሸባሪዎቹ ህውሓት  እና ሸኔ  በመቀናጀት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሰላም እንዳይኖር እየሰራ ይገኛል ያሉት ሃላፊው÷ የኦሮሞ ህዝብም የተገኘውን ድል ከሽብር ቡድኖቹ መጠበቅ አለበት ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
 
የክልሉ ወጣቶች ትናንት በባዶ እጃቸው ታንክ ፊት በመቆም ታግለው ወያኔን ከስልጣን እንዳስወገዱት ሁሉ ዛሬም በትናንቱ አቋማቸው ውሸታሙን እና ዘራፊውን ሃይል ሊታገሉት እንደሚገባ ጥሪ አቅርብዋል::
 
የክልሉ አርሶና አርብቶ አደሮችም ትናንት በጨለማ ውስጥ ሆናችሁ ዋጋ በመክፈል የመጣውን ለውጥ ልትጠብቁ ይገባል ነው ያሉት::
 
ሁሉም ህበረተሰብ የጠላተን ሴራ እና ጥፋት በመረዳት ሀገርን ለማፍረስ የተቃጣውን አደጋ በጋራ መመከት ይገባልም ብለዋል ::
 
የክልሉ ጸጥታ መዋቅር የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላትጋር በመቀናጀት ሰላሙን እንዲጠብቅ ጥሪ ማቅረባቸውን ኦ ቢ ኤን ዘግቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.