Fana: At a Speed of Life!

በጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ግድብ ውኃው ሳይፈስ ስኬታማ ጥገና ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ግድብ ውኃው ሳይፈስ ከ18 ሜትር ጥልቀት በላይ ወደ ውኃ ውስጥ በመግባት ስኬታማ ጥገና መከናወኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ንጉሴ ገለጹ፡፡
ግድቡ ላይ 1 ነጥብ 5 ሜትር ክበት ስንጥቅ በመኖሩ ግድቡ ውኃ የማስረግ ችግር ገጥሞት እንደነበር የገለፁት አቶ ደሳለኝ÷ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ውኃው ሳይፈስ ጥገናውን በማከናወን ችግሩን መቅረፍ ተችሏል፡፡
የቻይናው ሲ ጂ ጂ ሲ ኩባንያ የጥገና ሥራውን ያከናወነ ሲሆን÷ ውኃው ሳይፈስ በመጠገን ለኃይል ማመንጫው በቂ የውሃ ክምችት እንዲኖር አስችሏል ነው የተባለው፡፡
የደለል ማስወገጃና መቆጣጠሪያ አሸንዳ በጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቋርጦ የነበረ መሆኑን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ÷ ጥገና ተከናውኖለት ወደ ሥራ ለማስገባት የሙከራ እና የፍተሻ ሥራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል፡፡
ለጥገናው አጋዥ የሆኑ የመቆጣጠሪያ ሰሌዳ እና የሞተር ፓምፕ ገጠማ ሥራዎችም መከናወናቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በ1996 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የጊቤ አንድ የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ 184 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም አለው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.