Fana: At a Speed of Life!

የጅማ ዞን ማህበረሰብ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዞን ማህበረሰብ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ3 ሚሊየን ብር ባለይ የሚገመት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የጅማ ዞን ማህበረሰብ ለቦረና ዞን 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በድርቅ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ለእንስሳት የሚሆን ምግብ እና መኖ ነው ድጋፍ የተደረገው፡፡
‹‹እኛ እያለን የቦረና ህዝብ አይራብም›› በማለት የጅማ ዞን ነዋሪዎች ካላቸው ላይ ያሰባሰቡትን ድጋፍ ያስረከቡት የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር የተደረገውን ድጋፍ ለአባ ገዳዎች እና ለሀገር ሽማግሌዎች አስረክበዋል፡፡
በተመሳሳይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቦረና ዞን በድርቅ ምክንያት ለተጎዱና ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ግምቱ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ልዩ ልዩ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉም ምግብ ነክ፣ የቤት ቁሳቁስ፣ የከብቶች መኖ፣ አልባሳት እና ፍራሽ እንዲሁም ኮሮናን ለመከላከል የሚያስችሉ ማስክና ሳኒታይዘርን ያካተተ ነው፡፡
ችግሩ እስቀሚቀረፍ ድጋፉን እንደሚቀጥል ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተስፋሁን ከበደ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.