Fana: At a Speed of Life!

ወጣቱ ተደራጅቶ ወደ ግንባር በመዝመት ድል እያስመዘገበ እንደሚገኝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር በድኑን እኩይ ሴራ ለማክሸፍ የአካባቢው ወጣት ተደራጅቶ ወደ ግንባር እየዘመተ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ አኩሪ ድል እያስመዘገበ እንደሚገኝ የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አካሉ ወንድሙ ገለጹ።

ወጣቱ ባካሄደው ጠንካራ ትግል የመጣው ሀገራዊ ለውጥ በአሸባሪውና ሃገር አፍራሹ እብሪተኛ ቡድን እንዳይደናቀፍ ሴራውን በማክሸፍ የአባቶቹን ገድል ለመድገም የሚያደርገውን ተጋድሎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለመጣው ሃገራዊ ለውጥም ወጣቱ አይተኬ ሚና መጫወቱን ጠቅሰው ÷ አሁን ላይም የሽብር በድኑን እኩይ ሴራ ለማክሸፍ የአካባቢው ወጣት ተደራጅቶ ወደ ግንባር እየዘመተ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ አኩሪ ድል እያስመዘገበ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በደሴ ግንባር ባለው ግጭት ምክንያት በደብረ ብርሃን ከተማ የሰርጎ ገቦችን ስጋት ለመቀነስ በተደራጀ መልኩ ቀንና ሌሊት ወጣቶች እየጠበቁ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አሁን ሃገሪቱ ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ የዚህን ትውልድ መፍትሄ ይሻል ያሉት ምክትል ከንቲባው ÷ ለዚህም በአሸባሪው ቡድን ላይ ጠንካራ ክንዱን በማሳረፍ የድል ግስጋሴውን መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል።

የሽብር ቡድኑ የሚነዛውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ወደ ጎን በመተው መፍትሄው ላይ መረባረብ እንደሚገባ ጠቁመው፤ የክልሉ መንግስት በተደጋጋሚ ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ በመቀበል ወጣቱ በተግባር ምላሽ ሊሰጥ ይገባል ነው ያሉት አቶ አካሉ።

ለዚህም አቅሙ የፈቀደ የፀጥታ ሃይሉን በመቀላቀል ማገልገል እንዳለበትና አቅም የሌለው ደግሞ ህብረተሰቡን በማስተባበር የደጀንነት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሃገራችን አሁን ለመጣው ለውጥ የወጣቱ ትግል ላቅ ያለ ነው ያሉት ደግሞ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የልማትና የድጋፍ ማህበር የደብረ ብርሃንና አካባቢው አስተባባሪ መቶ አለቃ ሰለሞን ዘለቀ ናቸው።

”ወጣቱ ከስሜት በመውጣት ትክክለኛ ታሪኩን ከአባቶች ተረድቶ የበፊቱን የአንድነት፣ የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶችን እንዲቀጥሉ የአባቶቹን አደራ መወጣት አለበት” ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.