Fana: At a Speed of Life!

ሀገርን ለማዳን አንድነትን ማጠንከር ያስፈልጋል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ሀገርን ለማዳን ከመቼውም በላይ የአመለካከት እና ተግባር አንድነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

የሀረሪ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ ላይም የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ÷ በተለይም በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላቀ የአመለካከትና የተግባር አንድነት የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡

የአሸባሪው ህውሓትና ኦነግ ሸኔ አላማ ኢትዮጵያን ማፍረስ መሆኑን መገንዘብ እና መታገል ያስፈልጋል፡፡

አሸባሪው ህውሓት የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ጠላት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ ይህንንም ህዝብ እንዲረዳው ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስትና ህዝብም መከላከያ ሰራዊትን በሎጅስቲክና በሞራል መደገፍ የቀጣይ ቁልፍ ስራዎች መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

ሀገርን ከመታደግ ጎን ለጎንም እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ተግባራት ማጠናከር እንደሚገባም ጠቁመዋል ፡፡

እንዲሁም የሰራዊትን የሰው ሃይል ለማጠናከር በክልሉ የተጀመረው የመከላከያ ምልመላ በተጠናከረ መልኩ እንደሚካሄድ ነው የገለፁት፡፡

በተለይም ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የአካባቢን ሰላም ማስጠበቅ በትኩረት ይሰራል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል፡፡

እንደሀገር የገጠሙ ችግሮችን ለማለፍ በአንድነትና በሙሉ አቅም መረባረብ ይገባል ያሉት ደግሞ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ናቸው፡፡

በዋናነትም ሁሉም አካላት የአካባቢን ሰላም መጠበቅ ፣ መከላከያን መደገፍ እና ዘመቻውን መቀላቀል አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመደገፍ ስራም በትኩረት መሰራት አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ የተሳተፉ አመራሮችም የአሸባሪው ህውሓትን ሀገር የማፍረስ ተግባር ለመመከትና ሀገርን ለማዳን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናጋራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.