Fana: At a Speed of Life!

የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ክልሉ ላስተላለፈው ጥሪ የሚያበረታታ ምላሽ አሳይተዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ክልሉ ላስተላለፈው ጥሪ የሚያበረታታ ምላሽ ማሳየታቸውን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገለፀ፡፡

የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ከተማ አስተዳደሩ ከክልሉ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የግልና የመንግስት ታጣቂዎችን ምዝገባ እያካሄደ ሲሆን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል ተብሏል።

ከህብረተሰቡና ከአመራሩ ምን ይጠበቃል የሚለው ደግሞ በቀጣይ ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በፊት የሰለጠኑ የከተማው ወጣቶችም በጥሩ መነቃቃት ላይ ናቸው ብለዋል።

አመራሩም በመሪነት ዘመቻውን የሚመራ ሲሆን ÷ክልሉ እቅድ አዘጋጅቶ ወደስራ ገብቷል ፤ምንም አይነት ክፍተት በማይኖርበት ሁኔታም ይሰራል ነው ያሉት ከንቲባው።

በክልሉ የተጣለውን የሰአት እላፊ ማክበር የሁሉም ነዋሪ ሃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው፥ ይህም ብዙ ችግሮችን ለመቆጣጠር እንደሚረዳ አስረድተዋል።

በሰላም አስመላሽ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.