Fana: At a Speed of Life!

በኮንትሮባንድ የገቡ የተለያዩ ዕቃዎች ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንትሮባንድ የገቡ 71 ቦንዳ ጨርቅ፣ የተለያዩ ሽቶዎችና ቶርሽን ጫማዎች ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።
የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 99283 (አ.አ) አይሱዙ ተሽከርካሪ 30 ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ እና የተለያዩ ሽቶዎችን ጭኖ ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም. ሌሊት መነሻውን ኮንሶ አድርጎ ወደ ጂንካ ሲጓጓዝ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር አበባው እንዳለ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በበና ፀማይ ወረዳ ጎልዲያ ቀበሌ በቁጥጥር ስር የዋለው ይህንኑ እቃ ሲያጓጉዝ የነበረው አሽከርካሪ በተጠርጣሪነት መያዙን አስታውቀዋል።
ቀደም ሲልም÷ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 45652 (አ.አ) አይሱዙ ተሽከርካሪ 41 ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ እና አራት ማዳበሪያ ቶርሽን ጫማዎችን ጭኖ ተልተሌ ከተባለው አካበቢ ተነስቶ ሐመር ወረዳ እንደደረሰ ከነአሽከርካሪው መያዙን ገልጸዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.