Fana: At a Speed of Life!

ሰባት የኢፋ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሥራ ሊጀምሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳባት የኢፋ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የግንባታ ሥራቸውን አጠናቀው አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ በ2014 የትምህርት ዘመን 240 ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተገልጿል፡፡

ኢፋ ቦሩ ካስገነባቸው አዳሪ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሁለቱ የመማር ማስተማር ሥራ ቀደም ብለው የጀመሩ ሲሆን÷ በ2014 የትምህርት ዘመንም 7 አዳሪ ትምህርት ቤቶች በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎችን በመቀበል ለማስተማር መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡

በኦሮሚያ የተገነቡት የኢፋ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ለመማር ማስተማር ሂደቱ የሚያገለግሉ እና ሌሎች የትምህርት ቤት ቁሶችን ያሟሉ ናቸው ተብሏል፡፡

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ መገርቱ ሞሀመድ÷ ትምህርት ቤቶቹ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ሥራ ለመግባትም መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

ለተማሪዎቹ የምገባ አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞችም በምግብ ማብሰል እና በቤት አያያዝ ሰልጥነው ሥራ ለመጀመር ዝግጁ መሆናቸውን ተመላክቷል፡፡

የተማሪዎች ወላጆችም ምንም አይነት ስጋት ሳያድርባቸው ልጆቻቸውን ልከው እንዲያስተምሩ የቢሮ ኃላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ በቀጣይ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች መፍለቂያ እንዲሆኑ ታስቦ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የመግቢያ መስፈርቱን እና ፈተናውን የሚያሟሉ ተማሪዎችንም መንግስት ምግብን ጨምሮ ሌሎች ወጪዎችን ሁሉ እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡

በያደሳ ጌታቸው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.